የትግል ፍሬ ትዝታዬ

የወደፊት ቡድን Standing from left to right: Tesfaye Tilahun, Zewdu Takele, Aboneh mamo, Tsegaye, Berhe and Asrat Haile “Goradew”. Bottom row from left to right: Negussie Asfaw, Mengistu “EELPA”, Abdo Kedir, Shewangizaw and Tesfaye.

ይሄ ፅሁፍ ነው ረጅም ላንዳንዱ አሰልቺም ሊሆን ይችላል። እኔ ትዝታዬን ፅፌያለሁ። ስለፃፍኩትም ደስ ብሎኛል። ከቻላችሁ ሁሉንም አንብቡት፣ ካላቻላችሁ የቻላችሁትን እንብቡት፣ በጣም ካልቻላችሁ ግን ዝም ብላችሁ እለፉት) ይሄን ካልኩ በኋላ ይሄን ትዝታ ሁሉንም የሚጋራኝ ወንድሜና አብሮ አደግ ጓደኛዬ ኢሳያስ በዛን ጊዜ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አብሮኝ ስለነበር እሱደግሞ ቢጨምርበት ደስ ይለኛል። በፅሁፉ ላይ ግን ስህተት ያለ ከመሰላችሁ, የሚታረም ነገር ካገኛችሁ ጊዜው ረዝሟልና ነገር አምታትቼም ከሆነ ንገሩኘ፣ አርሙኝ። ጥያቄ ካላችሁም ደስ ብሎኝ እመልሳለሁ።

በኤርምያስ ብርሃነ

(ይሄ ፅሁፍ ነው ረጅም ላንዳንዱ አሰልቺም ሊሆን ይችላል። እኔ ትዝታዬን ፅፌያለሁ። ስለፃፍኩትም ደስ ብሎኛል። ከቻላችሁ ሁሉንም አንብቡት፣ ካላቻላችሁ የቻላችሁትን እንብቡት፣ በጣም ካልቻላችሁ ግን ዝም ብላችሁ እለፉት) ይሄን ካልኩ በኋላ ይሄን ትዝታ ሁሉንም የሚጋራኝ ወንድሜና አብሮ አደግ ጓደኛዬ ኢሳያስ በዛን ጊዜ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አብሮኝ ስለነበር እሱደግሞ ቢጨምርበት ደስ ይለኛል። በፅሁፉ ላይ ግን ስህተት ያለ ከመሰላችሁ, የሚታረም ነገር ካገኛችሁ ጊዜው ረዝሟልና ነገር አምታትቼም ከሆነ ንገሩኘ፣ አርሙኝ። ጥያቄ ካላችሁም ደስ ብሎኝ እመልሳለሁ።
አክባሪ ወንድማችሁ ኤርምያስ ብርሃነ)

ለረጅም ጊዜ እንደው ጊዜ አግኚቼ ስለ ትግል ፍሬ ትዝታዬ ፌስቡክ ላይ በፃፍኩ እያልኩ ከራሴ ጋር አወራ ነበረ። አሁን ጊዜ አገኘሁ። የምችለውን የማስታውሰውን ይኸው ፅፌያለሁ። የረሳሁትን በዛን ጊዜ አብሮኝ የነበረው አብሮ አደግ ጓደኛዬ ኢሳያስ ብርሃኑ ያስታውሰኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እንግዲህ የትግል ፍሬ የቡድኑንም ሆነ የተጫዋቾቹን ትጥቅ የምንይዘው ሶስት ነበርን። እኔ፣ ኢሳያስ እና የኢሳያስ ታላቅ ወንድም አበበ ነበርን። ጊዜውም 1972 ዓም ነበር። ትግል ፍሬ የተቋቋመው በ1971 ዓም ቢሆንም የተጠናከረውና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው በ1972 ዓም የመኢሰማ ቡድኖች በዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች ስር እንዲዋቀሩ ከተደረገ በኋላ። ትግል ፍሬ የሚጫወቱት ለምሳሌ በፉብሪካ፣ በመንገድ ስራ አውራ ጎዳና እና ህንፃ ኮንስተራክሽን መስሪያ ቤቶች የሚሰሩት ተጫዋቾች ነበሩ። የእርምጃችን ተጫዋቾች በመብራት ሃይል፣ በአስመጪና ላኪ፣ እና በሆቴሎች የሚሰሩት ሆኑ። በወደፊት ቡድን ውስጥ የሚጫወቱት ደግሞ በትራንስፖርት ፣ መድንና ባንክ የሚሰሩት ነበሩ። ይሄ አሰራር ሶስቱ ቡድኖች እንዲጠናከሩ በተለይም ትግል ፍሬ በጣም ተወዳጅ ሆኖ በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መፍረስ ምክኒያት ከስታዲዮም የሸሸውን ሰው ለማምጣት አስችሎት ነበር።

To read more, please visit Ermias’ Facebook Page

Share