ቅዱስ ጊዩርጊስ ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉን በተቀላቀለው ባህርዳር ከነማ ሸንፈትን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2011 (ኤፍቢሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎችና ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልል ከተሞች ተካሂደዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ዘንድሮ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ባህርዳር ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡

የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ካደረጉት አራት ቡድኖች መካከል ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ስሑል ሽረ ጨዋታውን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል፡፡

ሐዋሳ ላይ መከላከያን ያስተናገደው ደቡብ ፖሊስ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

የምሪምየር ሊጉን ሁለተኛ ጨዋታቸውን ካደረጉት ቡድኖች መካካል ደግሞ በፋሲለደስ ስታዲየም ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡

እንዲሁም በመቐለ ስታድየም ደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና 9 ሰዓት ላይ የተገናኙ ሲሆን በውጤቱም ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 1 በሆነ አሸንፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና መጀመሪያ ባደረገው ጨዋታ ድሬዳዋን አሸንፎ ሦስት ነጥብ መያዝ የቻለ ሲሆን ዛሬ ደደቢትን በማሸነፉ ነጥቡን ወደ ስድስት አድርሷል፡፡

በአንጻሩ ደደቢት ባደረጋቸው ሁለት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ትላንት መቐለ ላይ በተካሄደ አንድ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ወለዋሎን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታቱ ይታወሳል፡፡

Source: Fana Broadcasting

Share