Home » Ethiopian Soccer » የቦሌ መንገድ እጇን ለጊዮርጊስ ሰጠች

የቦሌ መንገድ እጇን ለጊዮርጊስ ሰጠች

በዘካርያስ ጌታቸው

ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ነው ንቅናቄው የተጀመረው። በቀነ እሁድ በመዲና እዲስ አበባ የመኪና ጥሩንባ፤ እልልታ፤ ጭፈራ የተለመደ ነው። ግንቦት 22ትን ያስተናገደችው ሰንበት ቀኗን በሰላም አሳልፋ ምሽቷ ላይ ለየት ያለ ክስተት አጋጥሟታል። ነጋሪት ስላልተነፋ፤ በሬድዮ ስላልተነገረ እንዲሁም በቴሌቪዥን ስላልተሰማ የከተሜ አዲስ አበባ ህዝብ ግራ የተጋባ ይመስላል። በእንዝርቷ መሃል በሚገኘው መስቀል አደባባይ ላይ ያልተለመደ ትዕይንት እየታየ ነው። ሞተረኞች ዓርማ ተሸክመው እና ተጊጠውበት ይሽከረከራሉ። በርካታ ሀይገር አውቶቡሶች በሰዎች ታጭቀዋል። አላፊው አግዳሚው በመገረም ትርIቱን ይመለከታል. . . እንዳንዱም የምሽቱ ትራንስፖርት እንዳያመልጠው ልቡን አደባባዩ ላይ ትቶ አካሉን መሄድ ወዳለበት እየወሰደ ነው…

ፈረሰኞቹ አዲስ አበባን ከለቀቁ ከአስራ አምስት ቀናት በላይ ሆኗቸዋል። የጉዞአቸው መሰረተ‐ዓላማ ታሪክን ለመስራት ነበርና በሩዋንዳ ሲካሄድ በነበረው የሲካፋ የክለቦች ውድድር ሁለተኛ በመውጣት ታሪክን መስራት የጠዋት እንጀራው ያደረገው አንጋፋው ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ክስተትን ይዞ ጉዞአቸውን ወደ መዲናችን ተያይዘውታል። ፈረሰኞቹን ይዞ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው አውሮፕላን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አዲስ አበባ እንደሚደርስ ተሰምቶአል። ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓትጀምሮ ሲጠነሰስ የነበረው ፕሮግራም ተሰካክቶ እነሆ አሁን እውን ሊሆን ነው።

ለብዙ ዓመታት የሀገራትን መሪዎች እእና ባለስልጣናትን በማስተናገድ የታወቀችው የቦሌ መንገድ ዛሬ በጊዮርጊሶች ተወራለች እጇንም ሰጥታለች። ከመስቀል አደባባይ የተነሳው ደጋፊ የራሱ ትራፊክ እና ፀጥታ አስከባሪ በመሆን በሞተረኛ በመታጀብ በመዝሙር በእልልታ … ሙሽራዬ አበባዬ እያለ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል። ቦሌ አይሮፕላን ማረፈያ ጆሮዋ የለመደው የሰማዩን ተሽከርካሪ ጩኅት ነው እንጂ በሌላ በሌላ ብዙም የሚደፍራት የለም። ዛሬ ጊዮርጊሶች አንበሳ ነን እኛእያሉ ፈረሰኞቹን ለመቀበል ቦሌን የጥምቀት ሜዳ አስመስለዋታል። የውጭ መንገደኛው ምነው ዛሬን ባገሬ ብታሳድረኝ የሚልም ይመስላል…

Read Full Report Here

4 Responses

  1. Beweketu Seyoum says:

    it appears a report on the battle of adwa……….tell z writer to go to school and learn ow to write stories….shameful

  2. abdi says:

    what does that means you make it like ethiopia won a world cup

    that team is ethiopia foot ball federation seporting more than our national team { this news is just madness when i read it i am think in { birtukan mideksa ) she going out of prison

  3. Really Great says:

    This is new history for Ethiopian football we should appreciate the team and we have to work hardly for participating in Africa too

  4. saints says:

    bewketu seyume coplexam.

Leave a Reply

© 2011 EthioSports · RSS · Designed by Theme Junkie · Powered by WordPress